የጳጉሜን ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 27/2017(ኢዜአ)፦የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት ዋዜማ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በተለያየ ዝግጅትና ስያሜ ለማክበር የዝግጅት ስራ መጠናቀቁን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ የ2018 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማ አምስቱ የጳጉሜን ወር ቀናት አከባበር ዝግጅትና ስያሜን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት መሸጋገሪያ አምስት የጳጉሜን ቀናትም በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።

በዚህም ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን፣ጳጉሜን 2 የህብር ቀን፣ ጳጉሜን 3 የእምርታ ቀን፣ ጳጉሜን 4 የማንሰራራት ቀን እና ጳጉሜን 5 የነገው ቀን በሚል እንደሚከበሩ ገልጸዋል።

ቀናቱም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚከበሩ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም