የጋምቤላ ክልልን ሰላም በማጽናት የህዝቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጥረት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል- ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ

ጋምቤላ ፤ነሐሴ 26/2017(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም በማጽናት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጥረት በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

በክልሉ አኮቦ ወረዳ ቀደም ሲል የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም፤ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጋምቤላ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።


 

በመድረኩ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድሯ በክልሉ ያለውን ሰላም በማጽናት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጥረት በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል ።

በክልሉ የተጀመሩ ልማት ስራዎችን በማፋጠን በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሰላም አጀንዳ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አንስተው በተለይም በክልሉ ጠረፋማ ወረዳዎች ሰላምን በማጠናከር የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

የኮንፈረንሱ ዓላማም በወረዳው በታለመው የሰላም ግንባታና ልማት ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ በመያዝ ለተግባራዊነቱ በጋራ ለመረባረብ በማሰብ ነው ብለዋል ።


 

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር)፤ የህዝቡን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ጠንክረንና ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም