የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት ምስረታ፣ የሥራ አስፈጻሚዎችና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ በስኬት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/ 2017(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት ምስረታ፣ የሥራ አስፈጻሚዎችና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ ጅብሪል ዑስማን ገለጹ።

የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ ጅብሪል ዑስማን ምርጫውን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ዛሬ የተካሄደው የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት ምስረታ፣ የሥራ አስፈጻሚዎች፣ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን አመላክተዋል።

በምርጫው የአዲስ አበባ መጅሊስን ለቀጣይ አምስት ዓመታት እንዲመሩ ሼኽ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን አስታውቀዋል።

በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ሼኽ ሙሐመድ ሸሪፍ የተመረጡ ሲሆን፤ ሼኽ ቡዲን ኑራን ዋና ጸሀፊ ሆነው መመረጣቸውንም ተናግረዋል።

ምርጫው ግልፅና ፍትሃዊ እንዲሁም ህዝባዊ ተሳትፎን ባረጋገጠ መልኩ መከናወኑን ገልጸዋል።

ምርጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማ አስተዳደሩ እና በየደረጃው ያሉ አካላት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም