ብራይተን ማንቼስተር ሲቲን አሸንፏል - ኢዜአ አማርኛ
ብራይተን ማንቼስተር ሲቲን አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2017 (ኢዜአ)፡- በሦስተኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በሜዳው ማንቼስተር ሲቲን ያስተናገደው ብራይተን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ሃላንድ የውኃ ሰማያዊዮቹን መሪ ያደረገች ግብ በ34ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ ወደ መልበሻ ክፍል ማምራት ችለው ነበር።
ሆኖም ከእረፍት መልስ ሚልነር በ67ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ብራይተንን አቻ ማድረግ የቻለች ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
እንዲሁም ግሩዳ በ89ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሮ፤ ብራይተን ሦስት ነጥብ ማሳካት ችሏል።
በሌላ የዛሬ መርሐ ግብር ዌስትሃምን ያስተናገደው ኖቲንግሃም ፎረስት 3 ለ 0 ተረትቷል።
የዌስተሃምን ግቦችም ቦውን በ84ኛው፣ ፓኩዌታ በፍጹም ቅጣት ምት በ88ኛው እንዲሁም ዊልሰን በ91ኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችለዋል።
ቀሪ የዛሬ መርሐ ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ፤ አመሻሽ 12 ከ30 የሣምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በሊቨርፑልና አርሰናል መካከል ይደረጋል።
እንዲሁም ምሽት 3 ሠዓት ላይ አስቶንቪላ ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።