የጋዜጠኛና ደራሲ የምወድሽ በቀለ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ - ኢዜአ አማርኛ
የጋዜጠኛና ደራሲ የምወድሽ በቀለ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/ 2017(ኢዜአ)፡- የጋዜጠኛ እና ደራሲ የምወድሽ በቀለ ሥርዓተ ቀብር ወዳጅ ዘመዶቿ እና የሙያ አጋሮቿ በተገኙበት አየር ጤና በሚገኘው ኪዳነ ምኅረት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።
የምወድሽ በድርሰትና ሥነ-ግጥም እንዲሁም በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎቿ ሀገሯን በማገልገል ትታወቃለች፡፡
በሕይወት ዘመኗ ባበረከተቻቸው አስተዋፅኦዎችም የ2016 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማትን ጨምሮ ሌሎች ዕውቅና እና ሽልማቶች አግኝታለች።
ደራሲ እና ጋዜጠኛ የምወድሽ በቀለ ባጋጠማት ህመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ዓርብ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ይታወቃል።