የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ተጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ተጀምሯል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2017(ኢዜአ)፦ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአበበ በቂላ ስታዲየም ተጀምሯል።
በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአሁኑ ሰዓት አርባምንጭ ከተማ ከይርጋጨፌ ቡና ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።
ሲዳማ ቡና ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጀመሪያ ሳምንት ከአዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ ሊያደርግ የነበረው ጨዋታ ቡድኑ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ተሳትፎው ምከንያት መራዘሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የንግድ ባንክ የሊጉ የመጀመሪያ ሶስት ጨዋታዎች በተስተካካይ መርሃ ግብር እንደሚያዙም አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
የውድድሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በሊጉ ላይ 14 ክለቦች ይሳተፋሉ።