የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት ምስረታ፣ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የሥራ አመራሮችና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት ምስረታና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የሥራ አመራሮችና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ በመካሄድ ላይ ነው።

የዛሬውን ምርጫ አስመልክቶ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ ጅብሪል ዑስማን መግለጫ ሰጥተዋል።


 

በመግለጫቸው የአዲስ አበባ መጅሊስ የምክር ቤት ምስረታና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የሥራ አመራሮችና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ምርጫ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ መጅሊስን ለቀጣይ አምስት አመታት የሚመሩ ፕሬዚዳንት የሚታወቁበት ቀን መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም