ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 24 /2017(ኢዜአ)፡-በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ በርንሌይን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብራያን ምቤሞ በጨዋታ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በፍጹም ቅጣት ምትና የበርንሌይ ተከላካይ ጆሽ ኩለን በራሱ ላይ ለዩናይትድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ፈርናንዴዝ በ97ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ግብ ወሳኝ ነበር።
ላይል ፎስተር እና ጄይደን አንቶኒ ለበርንሌይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረገው ማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታውን ሁለት ጊዜ እየመራ በተከላካይ ስህተት ግቦች ተቆጥረውበታል።
ውጤቱን ተከትሎ ዩናይትድ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን በማስመዝገብ በአራት ነጥብ 9ኛ ደረጃን ይዟል።
በርንሌይ በተመሳሳይ አራት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሌሎች ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 1 ለ 0፣ ኤቨርተን ዎልቭስን 3 ለ 2 እና ሰንደርላንድ ብሬንትፎርድን 2 ለ1 አሸንፈዋል።