ቀጥታ፡

የብር ሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የ42ኛ ዙር መሰረታዊ ወታደሮች አስመረቀ

ብር ሸለቆ፤ ነሐሴ 24/2017(ኢዜአ)፡ - የብር ሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የ42ኛ ዙር መሰረታዊ ወታደሮችን ዛሬ  አስመረቀ።

‎በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮንን እና ሌሎችም የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተዋል።

‎‎ሌተናል ጀኔራል ይመር  በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በኢትዮጵያ በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ፣ የላቀ ወታደራዊ አቅም ያለው ጠንካራ ሰራዊት መገንባቱን አንስተዋል።


 

ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ እሳቤ ነፃ ሆኖ ሀገርንና ሕዝብን የሚያገለግል አስተማማኝ የመከላከያ ሃይል መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።

ለዚህም መምሪያው በስሩ በሚገኙ የማሰልጠኛ ተቋማት ከመሰረታዊ ውትድርና እስከ አመራር አቅም በመገንባት ሂደት የላቀ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን አስታውሰው ፤ የዛሬው ምረቃም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል።

‎‎የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮሎኔል መኮንን መንግስቴ፤ትምህርት ቤቱ የሀገራችንን ሉአላዊነትና የሕዝባችንን ደህንነት በማስጠበቅ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ተቋም ነው ብለዋል።

‎የ42ኛ ዙር ተመራቂዎችን በስነ ልቦና፣ በአካል ብቃት፣  በቴክኒክና በስነ ምግባር በማነጽ  ለዛሬው ምርቃት ማብቃት መቻሉን ተናግረዋል።


 

‎‎የዛሬ ተመራቂዎችም በቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ከነባሩ የሰራዊት አባላት ጋር በመሆን በአገራችን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በማቃለል የበኩላቸውን  እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። 

‎በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮንን ጨምሮ ሌሎችም የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም