የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2017(ኢዜአ)፦የ2025/26 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ድልድል ዛሬ ማምሻውን በሞናኮ ይፋ ሆኗል።
ውድድሩ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ከባለፈው የውድድር ዓመት አንስቶ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ፎርማትን በማስቀረት 36 ክለቦች በ4 ቋቶች (Pots) በመከፋፈል እንዲጫወቱ የሚያደርግ አዲስ አሰራር መተግበር መጀመሩ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት 36ቱ ቡድኖች በ4 ቋቶች የተደለደሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ቋት 9 ክለቦች ይገኛሉ።
በቋት አንድ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ፣ ሪያል ማድሪድ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ባየር ሙኒክ፣ ሊቨርፑል፣ ኢንተር ሚላን፣ ቼልሲ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባርሴሎና ተደልድለዋል።
አርሰናል፣ ባየር ሌቨርኩሰን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ቤኔፊካ፣ አትላንታ፣ ቪያሪያል፣ ጁቬንቱስ፣ ኢንትራክት ፍራንክፈርት እና ክለብ ብሩዥ በቋት ሁለት የሚገኙ ናቸው።
በቋት ሶስት ቶተንሃም ሆትስፐርስ፣ ፒኤስቪ አይንድሆቨን፣ አያክስ፣ ናፖሊ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን፣ ኦሎምፒያኮስ፣ ስላቪያ ፕራግ፣ ቦዶ ግሊምት እና ማርሴይ ተገናኝተዋል።
ኮፐንሃገን፣ ሞናኮ፣ ጋለታሳራይ፣ ሴንት ዩኒየን ጊሎስ፣ ካራባግ፣ አትሌቲኮ ቢልባኦ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ፣ ፓፎስ እና ካይራት አልማቲ በቋት አራት የተደለደሉ ክለቦች ናቸው።
አንድ ክለብ በራሱ ቋት ካለ ሁለት ቡድንና በእያንዳንዱ ቋት ካሉ ሁለት ክለቦች ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
በዚህም አንድ ክለብ ስምንት ጨዋታ ያደርጋል።
ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ይገባሉ።
ቀሪዎቹ ስምንት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚገቡ ቡድኖች በሁለት የማጣሪያ ዙሮች ተጫውተው 16ት ውስጥ ይገባሉ።
ከጥሎ ማለፉ አንስቶ ያለው የውድድር ፎርማት ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው።
ከዚህ ቀደም በውድድሩ ላይ ይሳተፉ የነበሩ 32 ክለቦች በአሁኑ የውድድር አሰራር ወደ 36 ከፍ ማለታቸው ይታወቃል።