የቦትስዋና ምክትል ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2017(ኢዜአ)፦ የቦትስዋና ምክትል ፕሬዝዳንት ንዳባ ኒኮዚናቲ ጋዖላቲ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

በአዲስ አበባ ቆይታቸውም በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም