ቀጥታ፡

ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፈተች

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 21/2017(ኢዜአ)፦ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ በይፋ ከፍታለች።

በስነ ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ተገኝተዋል።


 

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ የኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።


 

ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ አድርገውት በነበረው የስራ ጉብኝት ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመክፈት መዘጋጀቷን ገልጸው ነበር።


 

ኢትዮጵያ እና ኮሎምቢያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1947 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም