ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2017(ኢዜአ)፦ ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ብሔራዊ ቡድኑ በፖላንድ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2026 ለሚካሄደው 12ኛው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያ ጋር መስከረም 11 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ ያደርጋል።
አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ እንዲሆኑ መሾማቸውን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ለአሰልጣኙ መልካም የሥራ ጊዜን ተመኝቷል።
በፖላንድ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2026 ለሚካሄደው 12ኛው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ።
አፍሪካ በውድድሩ ላይ አራት ሀገራት የማሳተፍ ኮታ ያገኘች ሲሆን ሀገራት በአራት ዙር የማጣሪያ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል።