የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19/2017(ኢዜአ)፦ የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
ምክትል ፕሬዚዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር የሁለቱ አገራት ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያና ኮሎምቢያ በ2015 ዓ.ም በፖለቲካ ምክክርና በሌሎች የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።
ሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እ.አ.አ በ1947 መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።