አርሰናል አዲስ አዳጊውን ሊድስ ዩናይትድ በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2017(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 5 ለ 0 ረቷል።


ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጁሪየን ቲምበር እና ቪክቶር ዮኮሬሽ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥሩ ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።


አዲስ ፈራሚው ዮኬሬሽ በአርሰናል ማልያ የመጀመሪያ ሁለት የሊግ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።


በጨዋታው አርሰናል ከፍተኛ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል።


ከክሪስታል ፓላስ ለአርሰናል የፈረመው ኢቤሬቺ ኤዘ ከጨዋታው በፊት ከደጋፊዎቹ ጋር ትውውቅ አድርጓል።


ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በስድስት ነጥብ የሊጉ መሪ ሆኗል።  አዲስ አዳጊው ሊድስ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።


ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ቶተንሃም ሆትስፐርስ  ከሜዳው ውጪ ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በርንሌይ ሰንደርላንድን 2 ለ 0 ሲረታ ቦርንማውዝ ዎልቭስን፣ ብሬንትፎርድ አስቶንቪላን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም