የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2017(ኢዜአ)፡- የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ ተካሄዷል።
በዚሁ መሰረት የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጀመሪያ ሳምንት ከሸገር ከተማ ይጫወታል።
ልደታ ክፍለ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ፣ አርባ ምንጭ ከተማ ከይርጋጨፌ ቡና፣ ባህር ዳር ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ከቦሌ ክፍለ ከተማ፣ መቻል ከኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ሌሎች የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብሮች መሆናቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የሚጀመር ሲሆን የመጀመሪያው ዙር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ሊጉ አስቀድሞ የሚጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከታንዛንያ ጋር ለሚያደርገው የመጨረሻ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ በቂ የዝግጅት ጊዜ እንዲያገኝ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።