ቀጥታ፡

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል በድምቀት መከበር ጀመረ

ሰቆጣና ወልዲያ፤ ነሀሴ 16/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞንና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በየዓመቱ ነሀሴ አጋማሽ ጀምሮ የሚከበረው የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል በዓል በደመቀ መልኩ መከበር ጀመረ። 

የሴቶች የነፃነት መገለጫ የሆነው የአሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓል በሰሜን ወሎ ዞንና በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች በድምቀት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ ህጻናት ሴቶች፣ ልጃገረዶች እና አዋቂ ሴቶች ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር በመሆን በባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች ተውበውና ደምቀው በየአደባባዩ ባህላዊ ጭፈራቸውን እየከወኑ ይገኛሉ።


 

ማህበረሰቡም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ባህላዊ መጠጥና ምግብ ለእንግዶች በማቅረብ የልጃገረዶቹን በዓል በማድመቅ ላይ ናቸው።

በበዓሉ ላይ የአካባቢው ማሀብረሰብና ሌሎች እንግዶችም መታደማቸው ታውቋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም