አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2017(ኢዜአ)፦ አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ከዚህ ቀደም የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ረዳት በመሆን እየሰሩ የነበሩት አሰልጣኝ ተመስገን ዳና በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ መሳይ ረዳታቸው በመሆን እንዲሰሩ አሰልጣኝ ደጉን መምረጣቸውን ገልጿል።
ፌዴሬሽኑ ለአሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ መልካም የሥራ ጊዜ ተመኝቷል።
የቀድሞ ምክትል አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ለሰጡት ግልጋሎት ምስጋናውን በማቅረብ በቀጣይ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው መልካም ነገር እንዲገጥማቸው ምኞቱን ገልጿል።