ታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ ከራስ ጥቅም በላይ ለአገር ሰርቶ ያለፈ አርአያ የሚሆን ሰው ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 13/2017(ኢዜአ)፦ታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ ከራስ ጥቅም በላይ ለአገር ሰርቶ ያለፈ አርአያ የሚሆን ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሸንካ ተናገሩ ።

የአንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ አስክሬን ሽኝት መርሃ-ግብር በብሄራዊ ቴአትር አዳራሽ እየተከሄደ ነው።

በሽኝቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ሚኒስትሮችና የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሚኒስትሯ  አርቲስት ደበበ ከኢትዮጵያ አልፎ በሆሊውድ ኢንዱስትሪ ትልቅ አሻራ ያሳረፈ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አርቲስት ደበበ በሙያው ስሙን የተከለ አንጋፋ የመድረክ ሰው ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አርቲስት ደበበ ከራስ ጥቅም በላይ ለአገር ጥቅም መስራትን በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

አርቲስት ደበበ በእውቀቱ እና በልምዱ ብዙ ማገልገሉን ገልጸው ለመላው ቤተሰብ እና ለሙያ አገሮቹ መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም