የታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 12/2017 (ኢዜአ)፦የታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
የታላቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ ሥርዓተ ቀብር በተመለከተ በብሔራዊ ቴአትር የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ ሰጥቷል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ /ጋሽ ደቤ/ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያኖረ አርቲስት እንደነበር ተገልጿል።
የታላቁ አርቲስት ስርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል።
ከዚያ በፊት አምስት ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የክብር ሽኝት እንደሚደረግለትም ታውቋል።
ደራሲ፣ ተርጓሚ፣አዘጋጅ እና ተዋናይ አርቲስት ደበበ እሸቱ የኢትዮጵያ ጥበብ አዘማኞች ትውልድ አካል ነበር።
በኢትዮጵያ ፍቅር የተጠመደ ወዳጆቿን የሚወድ፤ጠላቶቿን አብዝቶ የሚጠላ፤ በስራውና በሙያው የተመሰገነ አርቲስት መሆኑም ተገልጿል።