ቀጥታ፡

በተጠባቂው የሊግ ጨዋታ አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2017(ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር አርሰናል ማንችስተር ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በ13ኛው ደቂቃ ዴክላን ራይስ ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በግንባሩ በመግጨት ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ ሙከራ ተሽሎ ቢገኝም የአርሰናልን ተከላካይ መስመር ሰብሮ መግባት አልቻለም።

245ኛው ታሪካዊ የተቀናቃኞቹ ፍልሚያ በአርሰናል አሸናፊነት ተጠናቋል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች የአንደኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኖቲንግሃም ፎረስት ብሬንትፎርድን 3 ለ 1 ሲረታ ቼልሲ እና ክሪስታል ፓላስ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም