በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጅሊስ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል - ኢዜአ አማርኛ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጅሊስ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጅሊስ ምርጫ አሳታፊና ፍትሃዊነቱን በጠበቀ መልኩ ተከናውኖ በስኬት መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፉአድ መሐመድ ገለጹ።
ሀገር አቀፉ የመጅሊስ ምርጫ በዑለማዎች፣ በምሁራን፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና በሠራተኛ ማህበረሰብ ዘርፍ ከነሐሴ 9 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፉአድ መሐመድ የምርጫውን መጠናቀቅ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሲካሄድ የነበረው የመጅሊስ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ በ3ሺህ 921 ምርጫ ስፍራዎች የመጅሊስ ምርጫ መካሄዱን ገልጸው ምርጫው አሳታፊ በሆነ መልኩ መከናወኑን አንስተዋል።
ሙስሊሙ ማህበረሰብም በምርጫው በንቃት መሳተፉን ጠቁመዋል፡፡
መራጮች በበኩላቸው በምርጫው ግልጽ፣ ነጻና አሳታፊ በሆነ መንገድ ይመራናል ያሉትን አካል መምረጣቸውን ተናግረዋል፡፡