ኖቲንግሃም ፎረስት ብሬንትፎርድን ሲያሸንፍ ቼልሲ እና ክሪስታልፓላስ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኖቲንግሃም ፎረስት ብሬንትፎርድን ሲያሸንፍ ቼልሲ እና ክሪስታልፓላስ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2017 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታ ዛሬ በተመሳሳይ ሠዓት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
በዚህም መሠረት ኖቲንግሃም ፎረስት ብሬንትፎርድን ባስተናገደበት ጨዋታ 3 ለ 1 መርታት ችሏል።
የኖቲንግሃም ፎረስትን ግቦችም ክሪስ ውድ በ5ኛው እና በ48ኛው እንዲሁም ዳን ንዶዬ በ42ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
የብሬንትፎርድን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ቲያጎ በ78ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በሌላ ጨዋታ ቼልሲ ከክሪስታልፓላስ የተገናኙ ሲሆን፤ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው የፕሪሚየር ሊጉ የዛሬ መርሐ ግብር ሲቀጥል፤ ምሽት 12 ከ30 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን ያስተናግዳል።