አስቶንቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 10/2017 (ኢዜአ)፡-  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ አስቶንቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታው ኒውካስትል ዩናይትድ የነበረውን የኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል ወደ ጎል መቀየር ተስኖታል። አስቶንቪላ በጨዋታው ደካማ እንቅስቃሴ አሳይቷል። 

የአስቶንቪላው ተከላካይ ኢዝሪ ኮንሳ በ66ኛው ደቂቃ በአንቶኒ ጎርደን ላይ በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ቡድኑ ለ30 ደቂቃ በ10 ተጫዋች ለመጫወት ተገዷል። 

ኮንሳ በአዲሱ የውድድር ዓመት የቀይ ካርድ የተመለከተ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። 

ብራይተን ከፉልሃም፣ አዲስ አዳጊው ሰንደርላንድ ከዌስትሃም ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከበርንሌይ በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም