በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 10/2017 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

የዕለቱ የመክፈቻ መርሃ ግብር በአስቶንቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ መካከል ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 በቪላ ፓርክ ስታዲየም ይካሄዳል።

ወደ ሊቨርፑል የማምራት ከፍተኛ ፍላጎት ያሳደረው የኒውካስትል ዩናይትዱ አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳቅ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም። 

ተጫዋቹ በተያዘው ሳምንት ከዚህ በኋላ ለክለቡ መጫወት እንደማይፈልግ አሳውቋል።


 

ብራይተን ከፉልሃም፣ አዲስ አዳጊው ሰንደርላንድ ከዌስትሃም ዩናይትድ አና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከበርንሌይ በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

ዎልቨርሃምፕተን ዎንድረስ ከማንችስተር ሲቲ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በሞሊኒው ስታዲየም ይጫወታሉ።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት በተደረገው የመክፈቻ ጨዋታ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ቦርንማውዝን 4 ለ 2 አሸንፏል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ላጡት ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አንድሬ ሲልቫን በማሰብ ተጫዋቾች በክንዳቸው ላይ ጥቁር መለያ ጨርቅ በማሰር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም