ኒጀር እና ደቡብ አፍሪካ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 10/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና (ቻን) ምድብ ሶስት ኒጀር እና ደቡብ አፍሪካ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ትናንት ማምሻውን በማንዴላ ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደው መርሃ ግብር ደቡብ አፍሪካ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል በመፍጠር ብልጫ ብትወስድም ጎል ማስቆጠር አልቻለችም።

ውጤቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ በአምስት ነጥብ ሶስተኛ፣ ኒጀር በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በተያያዘም በዚሁ ምድብ በተደረገ ጨዋታ ጊኒ እና አልጄሪያ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም