ቀጥታ፡

የዑለማዎች ምርጫ አሳታፊነት ጠንካራ የእምነት ተቋም ግንባታን ለማስቀጠል መሰረት ይሆናል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2017(ኢዜአ)፦የዑለማዎች ምርጫ አሳታፊነት ጠንካራ የእምነት የተቋም ግንባታን ለማስቀጠል መሰረት እንደሚሆን የኢማሙ አህመድ አልጋዚ መስጂድ ምርጫ ጣቢያ የዑለማ ምርጫ ተሳታፊዎች ገለጹ።

የዑለማዎች ምርጫ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሠባት ዓለም ባንክ በሚገኘው የኢማሙ አህመድ አልጋዚ መስጂድ ምርጫ ጣቢያ ተካሄዷል።

የኢማም አህመድ አልጋዚ መስጂጅ ኢማም አብዱረኸማን መሀመድ እንዳሉት፤ የዑለማዎች የምርጫ ሂደት አሳታፊነና ግልጽነት በተሞላበት አግባብ መካሄዱን ገልጸዋል።


የዑለማዎች ምርጫ አሳታፊነትም በቀጣይነት ጠንካራ የእምነት ተቋም ግንባታን ለማስቀጠል መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል።

የኢማም አህመድ አልጋዚ መስጂጅ የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ ከድር ዑርጂ በበኩላቸው፤ የዑለማዎች ምርጫ የእምነት አስተምህሮ በሚፈቅደው አግባብ በሰላም መጠናቀቁ ለህዝበ ሙስሊሙ ወሳኝ ነው ብለዋል።

 




የኡለማ ምርጫ ተሳታፊዎች ህዝበ ሙስሊሙን ይመራሉ የሚላቸውን አባቶች መርጠዋል ያሉት ደግሞ የኢማም አህመድ አልጋዚ መስጂጅ የምርጫ አስፈፃሚ ምክትል ሰብሳቢ አብደላ ደልሰቦ ናቸው።


 

በኢማም አህመድ አልጋዚ መስጂጅ የምርጫ ተሳታፊ ፉዓድ ኑርዬ በበኩላቸው፤ ፍጹም አሳታፊ በሆነ አግባብ ይወክለኛል ብለው ያሰቡትን መምረጥ እንደቻሉ ተናግረዋል።


 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ ሂደቱን ጠብቆ የሚካሄደው የመጅሊስ የምርጫ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም