ጊኒ እና አልጄሪያ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጊኒ እና አልጄሪያ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና (ቻን) የምድብ ሶስት ጨዋታ ጊኒ እና አልጄሪያ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ካምፓላ በሚገኘው ማንዴላ ብሄራዊ ስታዲየም በተደረገው መርሃ ግብር ኢስማኤል ካማራ በ62ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ጊኒ መሪ መሆን ችላለች።
ጨዋታው በጊኒ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ሲባል ሶፊያን ባያዚድ በ88ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ለአልጄሪያ ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝታለች።
አልጄሪያ በጨዋታው ያገኘቻቸውን በርካታ የግብ እድሎች መጠቀም አልቻለችም።
ውጤቱን ተከትሎ አልጄሪያ በአምስት ነጥብ ሁለተኛ፣ ጊኒ በአራት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በዚሁ ምድብ ኒጀር ከደቡብ አፍሪካ ምሽት 2 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።