ቀጥታ፡

በድሬዳዋ አስተዳደር በሀገር አቀፍ የዑለማዎች ምርጫ ድምፅ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2017(ኢዜአ)፦በሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫ  በዑለማዎች ዘርፍ ምርጫ በድሬዳዋ አስተዳደር የድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት በመካሄድ ላይ ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወረዳ እስከ ፌደራል ድረስ ሂደቱን ጠብቆ የሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ መግለጹ ይታወቃል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በአራቱ የገጠር ክላስተር እና በዘጠኙ የከተማ ወረዳ በዑለማዎች ዘርፍ የድምፅ መስጠት ስነ-ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር በብዮ አዋሌ ክላስተር ብዮ አዋሌ እና ቢሻን በሄ ገጠር ቀበሌ  የዑላማዎች ምርጫ ድምጽ እየተሰጠ ነው። 

በሀገር አቀፍ ደረጃ የዘንድሮው የ2017 ዓ.ም መጅሊስ ምርጫ በ49 ሺህ 92 መስጅዶች 13 ሚሊዮን 151 ሺህ 889 ህዝበ ሙስሊም እንደሚሳተፍ ይጠበቃል። 

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም ድረስ የምሁራን፣ ወጣቶች ሴቶችና የስራ ማኅበራት ተወካዮች ምርጫ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም