ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝታለች

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 9/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) የምድብ አንድ መርሃ ግብር ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አንጎላን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

ትናንት ማምሻውን በማንዴላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጄፕቴ ኪታምባላ ቦላ እና ጆናታን ሞኮንዚ ካቱምቡዌ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

ውጤቱን ተከትሎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በስድስት ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ባላት ሞሮኮ በግብ ክፍያ ተበልጣ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። የሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሏን የተሻለ አድርጋለች። 

ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው አንጎላ በአራት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ሞሮኮ ዛምቢያን 3 ለ 1 አሸንፋለች።

ኬንያ ምድቡን በሰባት ነጥብ እየመራች ነው። 

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከሞሮኮ፣ ዛምቢያ ከኬንያ የሚያደርጓቸው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ወደ ሩብ ፍጻሜ የሚያልፉ ሁለት ሀገራትን ይለያሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም