በቻን ውድድር ሞሮኮ ዛምቢያን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በቻን ውድድር ሞሮኮ ዛምቢያን አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 8/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) የምድብ አንድ ጨዋታ ሞሮኮ ዛምቢያን 3 ለ 1 ረታለች።
በማንዴላ ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ራቤ ህሪማ፣ ኡሳማ ላምሉዊ እና ሳቢር ቡጅሪን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አንድሪው ፒሪ ለዛምቢያ የማስተዛዘኛዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ድሉን ተከትሎ ሞሮኮ በስድስት ነጥብ ከነበረችበት አራተኛ ደረጃ ወደ ሁለተኛ ከፍ ብላለች። ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሏንም አስፍታለች።
በውድድሩ ሶስተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ዛምቢያ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።
በዚሁ ምድብ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከአንጎላ ይጫወታሉ።