ቀጥታ፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫው ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 8/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫው ዝግጅት መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፉአድ መሐመድ ገለጹ።

ሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫ ከነገ እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኡለማዎች ዘርፍ፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሠራተኛ ማህበረሰብ ተወካይ ምርጫ የሚደረግ ይሆናል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፉአድ መሐመድ በክልሉ ለሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫ የተደረገውን ዝግጅት በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በክልሉ በ3 ሺህ 921 ቦታዎች ምርጫ እንደሚካሄድ ጠቁመው፤ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ለምርጫ መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ለመራጩ ህዝብ ስለ ምርጫ አፈጻጸም ግንዛቤ መሰጠቱን ጠቁመው፤ የምርጫ ቁሳቁሶች ዝግጅትም መጠናቀቁን ተናግረዋል።

‎ህዝበ ሙስሊሙ በሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫው የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም