ሞሪታኒያ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሏን ያሰፋችበትን ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች - ኢዜአ አማርኛ
ሞሪታኒያ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሏን ያሰፋችበትን ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 8/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) የምድብ ሁለት ጨዋታ ሞሪታኒያ ቡርኪናፋሶን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
ትናንት ማምሻውን በቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አላሳን ዲዮፕ በመጀመሪያው አጋማሽ ጭማሪ ደቂቃዎች ላይ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል።
የቡርኪናፋሶ የአማካይ ተጫዋች አብዱላዬ ቱሬ በ41ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ይህም ቡርኪናፋሶን ከእረፍት መልስ በ10 ተጫዋች እንድትጫወት አስገድዷታል።
ውጤቱን ተከትሎ በምድቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሞሪታኒያ ነጥቧን ወደ ሰባት ከፍ በማድረግ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሏን ሰፊ አድርጋለች።
በአንጻሩ ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ቡርኪናፋሶ በሶስት ነጥብ አራተኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን አንድ ጨዋታ እየቀራት ከውድድሩ ተሰናብታለች።
በዚሁ ምድብ በተካሄደ ሌላኛው ጨዋታ ማዳጋስካር ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን 2 ለ 0 አሸንፋለች።
ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ የምትመራው ታንዛንያ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፏ ይታወቃል።