ሴኔጋል እና ኮንጎ ብራዛቪል ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና(ቻን) በምድብ አራት መርሃ ግብር   ሴኔጋል እና ኮንጎ ብራዛቪል አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በቤንጃሚን ምካፓ ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዴቻን ሙሳቩ በ19ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኮንጎ ብራዛቪልን መሪ አድርጋ ነበር።

ይሁንና በ82ኛው ደቂቃ ጆሴፍ ላዩሴ ሳምብ ከመረብ ጋር ያገናኛት ጎል ለሴኔጋል ወሳኝ አንድ ነጥብ አስገኝታለች።

ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የቻን አሸናፊ ሴኔጋል በአራት ነጥብ በምድብ መሪነቷ ቀጥላለች። ኮንጎ ብራዛቪል በሁለት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ትከተላለች።

በዚሁ ምድብ ሱዳን ከናይጄሪያ ምሽት 2 ሰዓት በቤንጃሚን ምካፓ ብሄራዊ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም