ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ነሐሴ 25 ይጀመራል 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2017(ኢዜአ)፦ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ሊጉ አስቀድሞ የሚጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከታንዛንያ ጋር ለሚያደርገው የመጨረሻ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ በቂ የዝግጅት ጊዜ እንዲያገኝ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ገልጿል። 

ፌዴሬሽኑ ውድድሩን በተለያዩ ከተሞች የሚያካሂድበትን ፎርማት መቀየሩንና ክለቦች በሚያስመዘግቡት ሜዳ ጨዋታቸውን በደርሶ መልስ እንደሚያከናውኑ አመልክቷል። 

በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች የሜዳቸውን ጨዋታ የሚያደርጉበትን ሜዳ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያሳውቁም ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም