ቀጥታ፡

የጉምሩክ ኮሚሽንን በጠንካራ መዋቅር የማደራጀት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 5/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን በጠንካራ መዋቅር የማደራጀት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገለፁ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ ሰልጣኝ ሰራተኞችን አቀባበል በሚሊኒየም አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


 

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት የጉምሩክ ኮሚሽን ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ሥነ-ምግባር የተላበሱ እና ትጉ የሰው ሀይል ማፍራት፣ ዘመኑን የዋጁ አሰራሮችና ደንቦችን ማዘጋጀት እና ተቋሙን በቴክኖሎጂ የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽኑን በሰው ኃይል ይበልጥ ለማደራጀት ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ከሶስት ሺህ በላይ አዲስ ሰራተኞችን መቅጠሩን ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ ሥልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ሀገር ለምትሰጣቸው ተልዕኮ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ኮሚሽኑን በጠንካራ መዋቅር የማደራጀት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም