ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ሴቶች የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ሴቶች የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 4/2017(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲጎለብት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከኢትዮጵያ ሴቶች ልዩ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዕውቅናው የተሰጠው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የሴት አመራሮች የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመወከል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ሽልማቱን ተቀብለዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሴት አመራሮችን በማብቃት እና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ "የኢትዮጵያ ሴቶች ያመሰግኑሃል" የሚል የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት አበርክተዋል።