አንጎላ እና ኬንያ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1/2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና(ቻን) የምድብ አንድ ጨዋታ አንጎላ እና ኬንያ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

ማምሻውን በካሳራኒ ስታዲየም በተደረገው መርሃ ግብር ጆ ፓሴንሲያ በ7ኛው ደቂቃ  ባስቆጠራት ግብ አንጎላ መሪ ሆና ነበር።

ብዙም ሳይቆይ ኦስቲን ኦድሂያምቦ በ12ኛው ደቂቃ የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብ በመቀየር ኬንያን አቻ አድርጓል።

የኬንያው ማርቪን ኦሞንዲ በ21ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ ቡድኑ አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በ10 ተጫዋች ለመጫወት ተገዷል።

አንጎላ ባገኘችው የቁጥር ብልጫ ኳስ በመቆጣጣር በርካታ የግብ እድሎችን ብትፈጥርም ጠንካራውን የኬንያ የመከላከል አጥር ሰብራ መግባት አልቻለችም። 

ውጤቱን ተከትሎ ኬንያ በአራት ነጥብ በምድብ መሪነቷ ቀጥላለች።  አንጎላ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዛምቢያን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም