ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ አግኝታለች - ኢዜአ አማርኛ
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ አግኝታለች

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 1 /2017(ኢዜአ)፦ በስምንተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) የምድብ አንድ መርሃ ግብር ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዛምቢያን 2 ለ 0 አሸንፋለች።
በንያዮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢብራሂም ማቶቦ ሙላቡ በ51ኛው እና ማላንጋ ሆርሶ ምዋኩ በ71ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ የመጀመሪያ ድሏን ያስመዘገብችው የሁለት ጊዜ የቻን አሸናፊዋ ዴሞክራቲክ ሪፐሊክ ኮንጎ በሶስት ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።
ዛምቢያ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃ ይዛለች።
በዚሁ ምድብ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኬንያ ከአንጎላ በካሳራኒ ስታዲየም ይጫወታሉ።