በጠቅላይ መምሪያው የተሰሩ ሪፎርሞች የከተማዋን ዕድገት የሚመጥን የፖሊስ ተቋም እየተገነባ መሆኑን የሚያሳይ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በጠቅላይ መምሪያው የተሰሩ ሪፎርሞች የከተማዋን ዕድገት የሚመጥን የፖሊስ ተቋም እየተገነባ መሆኑን የሚያሳይ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሰሩ የሪፎርም ሥራዎች የከተማዋን ዕድገት የሚመጥን የፖሊስ ተቋም እየተገነባ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው በጠቅላይ መምሪያው የተከናወኑ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በጉብኝቱ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ እያከናወናቸው የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል አደረጃጀት፣ በሎጂስቲክ እና ምቹ የሥራ አካባቢ በመፍጠር ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።
ይህም የወንጀል መከላከል፣ ምርመራ እና የትራፊክ ቁጥጥር ሥራዎችን በተቀናጀ አግባብ ለመምራት የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
በጠቅላይ መምሪያው የተሰሩ የሪፎርም ሥራዎች የከተማዋን ዕድገት የሚመጥን የፖሊስ ተቋም እየተገነባ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑንም ተናግረዋል።
በቀጣይም የሪፎርም ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ነው ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ያስገነዘቡት።