ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀመረ

ሐረር ፤ ሐምሌ 28/2017(ኢዜአ)፦ ''ኃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለአብሮነት'' በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀመረ።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሰላም ጉባዔ ''ኃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለአብሮነት'' በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።


 

በጉባዔው ላይ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሮዛ ኡመር ፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሓፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት  ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተወካዮች፣ ከተለያዩ ክልሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።

በዚሁ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ላይ 300 የሚሆኑ የሁሉም ክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የታደሙ ሲሆን በኮንፍረንሱ ላይ ሁለት ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።


 

ከዚህ በተጨማሪ ተሳታፊዎቹ በሐረሪ ክልል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እና በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም