ቀጥታ፡

ዋልያዎቹ ድል ቀንቷቸዋል

 

አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 27/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 3 ለ 0 አሸንፏል።

ከእኩለ ሌሊት በአሜሪካ ኦውዲ ፊልድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ከነዓን ማርክነህ፣ ዳዋ ሆቴሳ እና ረመዳን የሱፍ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ብሄራዊ ቡድኑ ከተጋጣሚው የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።

ጨዋታውን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስታዲየሙ በመገኘት ተከታትለውታል።

ዋልያዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የ50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሽልማት ያገኛሉ። በተጨማሪም ወደ አሜሪካ አምርተው በመጫወታቸው 25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይበረከትለታል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ አምርቶ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማድረግ የሚያስችለውን የሶስት ዓመት ስምምነት ከዲሲ ዩናይትድ ጋር መፈራረሙ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም