የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቁ ፋይዳው የላቀ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ - ኢዜአ አማርኛ
የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቁ ፋይዳው የላቀ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
ኮምቦልቻ፤ሐምሌ 24/2017(ኢዜአ)፦የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቁ ለክልሉም ይሁን ለሀገር ፋይዳው የላቀ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወሎ ኮምቦልቻ የመንገደኞች አውሮፕላን ማስፋፊያ ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የኢትዮጵያ አየር መንግድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቁ ለክልሉም ይሁን ለሀገራዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በርካታ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑን አንስተው ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ይደረጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፥ የአየር ትራንስፖርቱን በማዘመንና ተደራሽነቱን በማስፋት የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በውጭና በሀገር ውስጥ መዳረሻውን እያሰፋ እና እየዘመነ መምጣቱን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በውጭና በሀገር ውስጥ መዳረሻውን እያሰፋ እና እየዘመነ መምጣቱን አንስተው፥ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ በአንድ ጊዜ 320 መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።
አየር መንገዱ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ ስድስት አዳዲስ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።