ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 20/2017(ኢዜአ)፦በዘላቂ የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት(ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ጉባኤ በአዲሰ አበባ በሚጀምርበት እለት የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት(ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ እላለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዘላቂ የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት።