የተመድ ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሀመድ የሥርዓት ምግብ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የተመድ ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሀመድ የሥርዓት ምግብ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2017(ኢዜአ)፦የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሀመድ በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የሥርዓት ምግብ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል
ምክትል ዋና ጸሀፊዋ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዴአታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ሁለተኛው የምግብ ስርአት ጉባኤ በኢትዮጵያ እና በጣሊያን የጋራ ጥምረት የተዘጋጀ ሲሆን ከሃምሌ 20 እስከ 22 2017 ዓ ም ድረስ ይካሄዳል።