የኢትዮጵያ ልዑክ በአፍሪካ ወጣቶች የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ ናይጄሪያ አመራ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/ 2017 (ኢዜአ)፦ በናይጄሪያ ሌጎስ በሚካሄደው የአፍሪካ ወጣቶች የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ስፍራው አቅንቷል።

ዓለም አቀፉ የጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን (ITTF) ያዘጋጀው ሻምፒዮና ከሐምሌ 20 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ይደረጋል።

በሁለቱ ጾታዎች ስምንት ስፖርተኞች ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።


 

ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ የምትሳተፈው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። 

ሻምፒዮናው ለስፖርተኞቹ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት እድገት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ልዑካን ቡድኑ በሻምፒዮናው ላይ መልካም ውጤት እንዲገጥመው ተመኝቷል። 

በአፍሪካ ወጣቶች የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና 27 ሀገራት ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም