ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ አመርቂ ድሎችን አስመዝግቧል-ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ አመርቂ ድሎችን ማስመዝገቡን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዕቅድና በተቋሙ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።


 

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት፤ተቋሙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የአምስት ዓመቱ የስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸሙም ስኬታማ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነር ጀነራሉ፥ በመጪው አምስት ዓመታትም ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢኮኖሚ፣ፖለቲካ፣ ዲፕሎማሲ፣በጸጥታ፣በዲጂታል እና በሌሎችም ዘርፎች አመርቂ ድሎች ማስመዝገቧን አንስተዋል።

ለድሎቹ መገኘትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ በርካታ ድሎችን ማስመዝገቡንም ገልጸዋል።

በቀጣይም ሀገር የያዘቻቸው የልማት ዕቅዶች በውጤታማነት እንዲከናወኑ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እንደሚወጣም ተናግረዋል።


 

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሀገርን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ሀገር በሁሉም ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም እንድታስመዘግብ የማድረግ ሃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም እንዲሁ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም