ሞሮኮ ለፍጻሜ ደረሰች - ኢዜአ አማርኛ
ሞሮኮ ለፍጻሜ ደረሰች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 15/ 2017 (ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ሞሮኮ ጋናን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፋለች።
ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስቴላ ንያሜኬዬ በ26ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ ጋና መሪ ሆና ነበር።
ከእረፍት መልስ ሳኪና ኡዝራዊ በ55ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ጎል ሞሮኮን አቻ አድርጋለች።
ጨዋታው በመደበኛ 90 ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርቷል።
በጭማሪ 30 ደቂቃ ግብ ባለመቆጠሩ አሸናፊውን በመለያ ምት መለየት ግድ ሆኗል።
በዚህም አዘጋጇ ሞሮኮ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሳለች።
በፍጻሜው ከናይጄሪያ ጋር ትጫወታለች። የፍጻሜው ጨዋታ ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
ዛሬ በተደረገው የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ናይጄሪያ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
የግማሽ ፍጻሜ ተሸናፊዎቹ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት አርብ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ይጫወታሉ።