ጤናው የተጠበቀ እና አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመው ብልፅግና ወሳኝ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2017(ኢዜአ)፦ ጤናው የተጠበቀ እና አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመው ብልፅግና ወሳኝ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ትናንት የተጀመረው የከተማ አስተዳደሩ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል፡፡

ከ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ ግምገማ እና ከ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ጎን ለጎን ዛሬ ጠዋት ሁሉም አመራሮች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ማከናወናቸውን የኤፍ ኤም ሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡


 


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት ጤናው የተጠበቀ እና አካሉ የዳበረ አመራር ለምናልመው ብልፅግና ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም