የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ደቡብ አፍሪካ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2017(ኢዜአ)፦ በ13ኛው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ሴኔጋልን በመለያ ምት በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፋለች።

ማምሻውን በሆነር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ምንም ግብ ባለመቆጠሩ 30 ደቂቃ ተጨምሯል። 

በጭማሪው ሰዓት የውጤት ለውጥ ባለመኖሩ ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል።

ደቡብ አፍሪካ በመለያ ምት 4 ለ 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። ለፍጻሜው ለማለፍ ከናይጄሪያ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ደቡብ አፍሪካ የወቅቱ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ናት።

ሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ እና ጋናን ያገናኛል።

የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም